ወላይታ ድቻ 2-1 ኢትዮጵያ ቡና
6′ በዛብህ መለዮ
፡ 90+5′ ኤፍሬም ወንድወሰን (በራሱ ግብ ላይ)
13′ አብዱልከሪም መሃመድ
– – – – –
* ቦዲቲ ስታድየም የተደበላለቁ ስሜቶች እያስተናገደ ይገኛል፡፡ ቡናዎች በሃዘን ድቻዎች በከፍተኛ ደስታ ላይ ይገኛሉ፡፡
ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በድቻ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
90+5 ጎልልል!!! ድቻ
ኤፍሬም በራሱ ግብ ላይ አስቆጠረ
* ጨዋታው በድጋሚ ጀምሯል፡፡
* ጨዋታው ቆሟል፡፡ አርቢቴር ይርጋለም ፍፁም ቅጣት ምት ከልክሎናል በሚል የድቻ ደጋፊዎች ድንጋይ መወርወር ጀምሯል፡፡
90′ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
87′ ድቻዎች የማሸነፍያ ጎል ፍለጋ በተደጋጋሚ የቡና የግብ ክልል በመድረስ ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡
84′ አላዛር እጅግ እጅግ ለግብ የቀረበ ኳስ ሞክሮ ሀሪሰን እንደምንም አውጥቶበታል፡፡
81′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
ኢኮ ፊቨር ገብቶ ዊልያም ያቤውን ገብቷል፡፡
81′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
አማኑኤል ተሾመ ወጥቶ ስንታየሁ መንግስቱ ገብቷል፡፡
79′ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ በግብ ጠባቂው የአቋቋም ስህተተ አላዛር ቢያገኘውም ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
78′ እያሱ ያሻገረለትን ኳስ አማኑኤለ ልመሬት ለመሬት አክርሮ መትቶ ወንድወሰን ይዞበታል፡፡
72′ ፓትሪክ ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ ቢያገኝም ግብ ጠባቂው ተደርቦ አውጥቶበታል፡፡
71′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
አናጋው ባደግ ወጥቶ ሰለሞን ሀብቴ ገብቷል፡፡
* ጥላሁን እና ኤልያስ የአሰልጣኙን ቅያሪ በመቃወም ሰላምታ ሳይሰጡ ተቀምጠዋል፡፡
66′ የተጫዋች ለውጥ – ቡና
ጥላሁን ወልዴ እና ኤልያስ ማሞ ወጥተው ፓትሪክ እና አማኑኤል ዮሃንስ ገብተዋል፡፡
64′ በድሉ መርዕደ ድየጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመዞበታል፡፡
62′ ፀጋዬ ከፍፁም ቅጣት ምት ጠርዝ የመታውን ኳስ የቡና ተከላካዮች ተረባርበው አውጥተውታል፡፡
59′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
በዛብህ መለዮ ወጥቶ ፀጋዬ ብርሃኑ ገብቷል፡፡
47′ ያቤውን ዊልያም ወደ መስመር በመውጣት ያሻማው ኳስ አቅጣጫውን ቀይሮ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ወደውጪ ወጥቷል፡፡
ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ
– – – –
ተጠናቀቀ
የመጀመርያው አጋማሽ 1-1 ተጠናቋል፡፡
45′ የጨዋታው የመጀመርያ አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
– ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች ወደ ጎል ለመድረስ ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡
13′ ጎልልል!!! ኢትዮጵያ ቡና
አብዱልከሪም መሃመድ በራሱ ጥረት ከመስመር ወደውስጥ በመግባት ግብ አሰቆጥሮ ቡናን አቻ አድርጓል፡፡
8′ አብዱልከሪም ያሻገረውን ኳስ ወንድወሰን በአግባቡ መያዝ ባለመቻሉ እያሱ አግኝቶ አገባው ተብሎ ሲጠበቅ ቶማስ ስምረቱ አውጥቶበታል፡፡
6′ ጎልልል!!! ወላይታ ድቻ
አላዛር ቡናን የጨዋታ ውጪ መስመር ጥሶ ያሻገረለትን ኳስ በዛብህ መለዮ በግንባሩ በመግጨት ድቻን ቀዳሚ አድርጓል፡፡
1′ ጨዋታው ተጀመረ
– – – – – – – – – – –
የወላይታ ድቻ አሰላለፍ
ወንድወሰን አሸናፊ
አናጋው ባደግ – ሙባረክ ሽኩሪ – ቶማስ ስምረቱ – ፈቱዲን ጀማል
አማኑኤል ተሾመ – ዮሴፍ ድንገቱ – በድሉ መርዕድ – መሳይ አንጪሶ – በዛብህ መለዮ
አላዛር ፋሲካ
– – – –
የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
ሀሪሰን ሀሶው
አብዱልከሪም መሀመድ – ወንድይፍራው ጌታሁን ኤፍሬም ወንድወሰን- ሳለአምላክ ተገኝ
ጋቶች ፓኖም – መስኡድ መሃመድ – ኤልያስ ማሞ
ጥላሁን ወልዴ – ያቤውን ዊልያም – እያሱ ታምሩ