መከላከያ ከ አዳማ ከተማ ፡ ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

መከላከያ 1-0 አዳማ ከተማ
32′ ቴዎድሮስ በቀለ
– – – –

ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በመከላከያ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ

90′ ተጨማሪ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

82′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
ባዬ ገዛኸኝ ገብቶ ሙሉአለመ ምጥላሁን ወጥቷል፡፡

* የአዳማ ከተማ ደጋፊዎች አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ላይ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡

76′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
ቴዎድሮስ ታፈሰ ገብቶ መሃመድ ናስር ወጥቷል፡፡

74′ የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
ጫላ ድሪባ ገብቶ ሻኪሩ ወጥቷል፡፡

68′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
ሳሙኤል ሳሊሶ ወጥቶ ማራኪ ወርቁ ገብቷል፡፡

63′ ሙሉአለም በጥሩ ሁኔታ ያቀበለውን ኳስ ፍሬው ሞክሮ ጃኮብ እንደምንም ይዞበታል፡፡

58′ ከማዕን ምት የተሻገረውን ኳስ ወንድወሰን ሚልኪያስ በግንባሩ ገጭቶ ጀማል ጣሰው አውጥቶበታል፡፡

49′ አዲሱ ተስፋዬ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

47′ ሱሌማን ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ሻኪሩ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ለውጥ – ብሩክ ቃልቦሬ ወጥቶ ቢንያም አየለ ገብቷል፡፡
– – – –

ተጠናቀቀ
የመጀመርያው አጋማሽ በመከላከያ 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

32′ ጎልልል!!! መከላከያ
ቴዎድሮስ በቀለ በግራ መስመር ከመሃመድ ናስር የተሻገረለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አሳርፏል፡፡

30′ የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
ታፈሰ ተስፋዬ ወጥቶ ወንድሜነህ ዘሪሁን

24′ መከላከያ በረጅሙ የአዳማ የግብ ክልል ለመድረስ ከሚያደርገው ጥረት በቀር ሁለቱም ቡድኖች የተደራጀ እንቅስቃሴ ማሳየት አልቻለም፡፡

*ጀማል ጣሰው ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ቋሚ አሰላለፍ ተመልሶ እየተጫወተ ሲሆን ተስፋዬ አምና የተጫወተበት መከላከያን በተቃራኒው እየገጠመ ይገኛል፡፡

16′ ሱሌማን የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመዞበታል፡፡

15′ መሃመድ ናስር የፍፁም ቅጣት ምቱን መትቶ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል፡፡

13′ ጃኮብ መሃመድ ናስርን በመጥለፉ ለመከላከያ የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡ ጃኮብም የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመዞበታል፡፡

3′ ሻኪሩ ከፍፁም ቅጣት ምት የቀኝ መስመር የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

1′ ጨዋታው ተጀመረ



 

የመከላከያ አሰላለፍ

ጀማል ጣሰው

ነጂብ ሳኒ – አዲሱ ተስፋዬ – ሙሉቀን ደሳለኝ – ቴዎድሮስ ወርቁ

ሚካኤል ደስታ – በሃይሉ ግርማ – ፍሬው ሰለሞን – ሳሙኤል ሳሊሶ

ሙሉአለም ጥላሁን – መሃመድ ናስር

—–

የአዳማ ከተማ አሰላለፍ

ጃኮብ ፔንዛ

እሸቱ መና – ተስፋዬ በቀለ – ሞገስ ታደሰ – ሱሌማን መሃመድ

ብሩክ ቃለቦሬ – ወንድወሰን ሚልኪያስ – ፋሲካ አስፋው

ታከለ አለማየሁ – ታፈሰ ተስፋዬ – አቢኮዬ ሻኪሩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *