ኢትዮጵያ ቡና የአጥቂውን ውል አድሷል

በዝውውር ገበያው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች የአጥቂያቸውን ውል አድሰዋል።

በአሠልጣኝ ካሳዬ አራጌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በቀጣዩ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዓመት እና በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ተጠናክሮ ለመቅረብ አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረሙ ይገኛሉ። አዲስ ተጫዋቾች ቡድኑን ከመቀላቀላቸው በተጨማሪም ክለቡ የነባር ተጫዋቾችን ውል እያደሰ ይገኛል።

ክለቡ አሁን ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረትም ዓምና ቡናማዎቹን የተቀላቀለው እንዳለ ደባልቄ እስከ 2016 ድረስ ለመቆየት የሦስት ዓመት ውል ፈርሟል። ከአምናው አንፃር ዘንድሮ ብዙ ደቂቃ ያልተጫወተው የቀድሞ የደደቢት፣ ሀዲያ ሆሳዕና፣ ጅማ አባጅፋር እና ባህር ዳር ከተማ አጥቂ ዘንድሮ በተጫወተባቸው 181 ደቂቃዎች አንድ ጎል ሲያስቆጥር ሁለት ጎል የሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ አቀብሏል።