በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተከናወነ የሚገኘው የሴካፋ ውድድር የሰዓት ሽግሽግ እንደተደረገበት ታውቋል።
ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ጊዜ የምታስተናግደው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሐምሌ 10 ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሆነ ይታወቃል። እርግጥ በባህር ዳር አመሻሽ ላይ እየጣለ ያለው ዝናብ ውድድሩን ትንሽ ያደበዘዘው ቢመስልም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና ሴካፋ የውድድሩ የመስል መብት ካለው አዛም ቲቪ ጋር ተነጋግረው የጨዋታዎች የሰዓት ማሻሻያ አድርገዋል። በዚህም ዛሬ የሚደረገው የኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ከ10 ሰዓት ወደ 8 ሰዓት የዞረ ሲሆነ ከነገ ጀምሮ የሚደረጉት ጨዋታዎችም በሙሉ የሰዓት ለውጥ ተደርጎባቸዋል። ከነገ ጀምሮ የሚደረጉት እና ለውጥ የተደረገባቸው አዲስ የውድድሩ መርሐ-ግብሮች የሚከተሉት ናቸው።
ሐምሌ 17 (ቅዳሜ)
ጨዋታ 8 – ጂቡቲ ከደቡብ ሱዳን (5:45)
ጨዋታ 9 – ዩጋንዳ ከታንዛኒያ (8:00)
ሐምሌ 19 (ሰኞ) ደረጃ ለመለየት የሚደረጉ ጨዋታዎች
ጨዋታ 10 – 5ኛ የወጣው ቡድን ከ8ኛ ከወጣው ቡድን (5:45)
ጨዋታ 11 – 6ኛ የወጣው ቡድን ከ7ኛ ከወጣው ቡድን (8:00)
ሐምሌ 20 (ማክሰኞ) የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች
ጨዋታ 12 – የምድብ 1 አሸናፊ ከምርጥ 2ኛ ቡድን (5:45)
ጨዋታ 13 – የምድብ 2 አሸናፊ ከምድብ 3 አሸናፊ (8:00)
ሐምሌ 22 (ሐሙስ) ደረጃ ለመለየት የሚደረጉ ጨዋታዎች
ጨዋታ 14 – (7ኛ እና 8ኛ ቦታን ለመያዝ) የጨዋታ 10 ተሸናፊ ከጨዋታ 11 ተሸናፊ (5:45)
ጨዋታ 15 – (5ኛ እና 6ኛ ቦታን ለመያዝ) የጨዋታ 10 አሸናፊ ከጨዋታ 11 አሸናፊ (8:00)
ሐምሌ 23 (ዓርብ)
ጨዋታ 16 – (ለ3ኛ ደረጃ) የጨዋታ 12 ተሸናፊ ከጨዋታ 13 ተሸናፊ (5:45)
ጨዋታ 17 – (የፍፃሜ) የጨዋታ 12 አሸናፊ ከጨዋታ 13 አሸናፊ (8:00)