የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርአት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል

አርባ ስድስት ክለቦችን ተሳታፊ እንደሚያደርግ የተረጋገጠው እና በአስራ አንድ ምድቦች ተከፍሎ በነገው ዕለት የሚጀመረው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡

የ2013 የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከሐምሌ 18 እስከ ነሀሴ 23 ድረስ በሀዋሳ ከተማ አስተናጋጅነት ከነገ ጀምሮ በሚደረጉ ጨዋታዎች መከናወን ይጀምራል፡፡ ከነገ የመክፈቻ ጨዋታዎች በፊት በዛሬው ዕለት የፌዴሬሽን ተወካዮች፣ የክለብ አመራሮች እና የተለያዩ የኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዕጣው በሀዋሳ ሚሊኒየም አዳራሽ ወጥቷል፡፡ ዕጣው ይወጣል ተብሎ አስቀድሞ የተባለው የባህል አዳራሽ ባልታወቀ ምክንያት በድንገት በመለወጡ ፕሮግራሙ ከተያዘለት ሰአት ዘጠኝ ሰዓታትን ዘግይቶ አስር ሰአት ሲል ጀምሮ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ የደንብ ውይይት እና የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርአት ከተካሄደ በኋላ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ አስቀድሞ አቶ ከበደ ወርቁ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የውድድር ዳይሬክተር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር አማካኝነት የዕለቱ ፕሮግራም ተጀምሯል፡፡

ዳይሬክተሩ የመክፈቻ ንግግር እና ስለውድድሩ ዓላማው ካስተረዱ በኋላ በተለያየ መልኩ የተዋቀሩት ኮሚቴዎች አጫጭር ማብራሪያ ለክለቦች እንዲያስረዱ ሆኗል። የውድድሩ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ የሺዋስ ለውድድሩ የተዘጋጀውን ደንብ በዝርዝር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በመቀጠል አቶ ብዙአየው የውድድሩ ሰብሳቢ በቀረበው ደንብ ላይ ክለቦች ያነሱትን ጥያቄ ምላሽ ሰጥተው ስለ ምድብ ድልድሉ ገለፃ ተደርጓል፡፡

ለውድድሩ አምስት ሜዳዎች የተዘጋጁ ሲሆን ለልምምድ ደግሞ 12 ሜዳዎች እንደተዘጋጁ አቶ ከበደ ወርቁ የፌዴሬሽኑ የውድድር ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡ 46 ቡድኖችን ተካፋይ የሚያደርገው እና በ11 ምድቦች የተከፈለው የምድብ ድልድል አምስት አምስት ቡድኖች ካሉበት ቡድን ሁለት ሁለት ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፉ ሲሆን ከዘጠኙ ምድቦች ደግሞ አንድ አንደኛ ሆነው የሚጨርሱ ክለቦች ወደ ሩብ ፍፃሜው የሚሸጋገሩ ይሆናል ተብሏል፡፡ የምድብ ማጣሪያው ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ አስራ ስድስት ውስጥ የሚያልፉ ክለቦች ጨዋታ ካደረጉ በኋላ አሸናፊ ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ወደ 2014 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ማለፋቸውን የሚያረጋግጡ ሲሆን ተሸናፊ የሆኑ ቀሪ ስምንት ቡድኖች እርስ በእርስ ተገናኝተው አሸናፊ የሚሆኑ አራት ክለቦች በተመሳሳይ ወደ አንደኛ ሊግ ማደጋቸውን የሚያረጋግጡ እንደሆነ ተብራርቷል። በአጠቃላይ በድምሩ 12 ክለቦች አላፊ ይሆናሉ በማለት በእለቱ ገለፃ ተደርጓል፡፡ ውይይቶቹ ከተጠናቀቁ በኃላ የምድብ ድልድል ተከናውኗል፡፡

ምድብ ሀ

1. ቦዲቲ ከተማ ( ከደቡብ ክልል)

2. ኩርሙክ ከተማ (ከቤንሻንጉል ጉሙዝ)

3. ኢታንግ ከተማ (ከጋምቤላ ክልል)

4. ጉንዶ መስቀል ከተማ (ከኦሮሚያ)

5. ቡሬ ዳሞት (አማራ ክልል

ምድብ ለ

1.አሳይታ ወረዳ (አፋር ክልል)

2. ኑዌር ዞን (ጋምቤላ ክልል)

3. አሊ ሀብቴ ጋራዥ (ድሬዳዋ)

4. ደምቦያ ወረዳ (ደቡብ ክልል)

5. ወንዶ ገነት ወረዳ (ሲዳማ ክልል)

ምድብ ሐ

1. ገንደ ሸቤል (ድሬዳዋ)

2. አቃቂ ማዞሪያ (አዲስ አበባ)

3. ቡሳ ከተማ (ኦሮሚያ ክልል)

4. ሠመራ ሎጊያ (አፋር ክልል)

ምድብ መ

1. ሐረር ዩናይትድ (ሐረር ክልል)

2. አመያ ወረዳ (ኦሮሚያ ክልል)

3. ቦንጋ መምህራን ኮሌጅ (ደቡብ ክልል)

4. ቫርኔሮ ወረዳ 16 (አዲስ አበባ)

ምድብ ሰ

1. ካማሺ ከተማ (ቤ/ጉሙዝ ክልል)

2. ሀሁ አዲስ ከተማ (ሀዋሳ ሲዳማ)

3. ሊሙ ገነት ከተማ (ኦሮሚያ ክልል)

4. ዋልያ ድሬ (ድሬዳዋ)

ምድብ ረ

1. ቦሌ ክፍለ ከተማ (አዲስ አበባ)

2. አማራ ሳይንት (አማራ ክልል)

3. ጋርዱላ ክለብ (ደቡብ ክልል)

4. ድሬዳዋ  ቀበሌ 06 (ድሬዳዋ)

ምድብ ሠ

1. አዲስ ቅዳም (አማራ ክልል)

2. አለታ ወንዶ ከተማ (ሲዳማ ክልል)

3. አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ (አ/አበባ)

4. ገንደ ተስፋ (ድሬዳዋ)

ምድብ ሸ

1. ጋምቤላ ዩንቨርስቲ (ጋምቤላ ክልል)

2. መንጌ ቤንሻንጉል (ቤ/ጉሙዝ ክልል)

3. ምህረት ክለብ (አዲስ አበባ)

4. ዋግዕምራ (አማራ ክልል)

ምድብ ቀ

1. ምስራቅ ክፍለ ከተማ (ሲዳማ ሀዋሳ)

2. ጋምቤላ አብይ አካዳሚ (ጋምቤላ ክልል)

3. ሸንኮር ወረዳ (ሐረር ክልል)

4. ዱብቲ ወረዳ (አፋር ክልል)

ምድብ በ

1. ዱከም ከተማ (ኦሮሚያ ክልል)

2. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ (ቤ/ጉሙዝ)

3. አለታ ጪኮ (ሲዳማ ክልል)

4. ዱራሜ ከተማ (ደቡብ ክልል)

ምድብ ተ

1. ካራማራ ክለብ (ሶማሌ ክልል)

2. ዱብቲ ከተማ (አፋር ክልል)

3. ወረኢሉ ለገሂዳ (አማራ ክልል)

4.ሐረር ፖሊስ (ሐረር ክልል)

አስራ ስድስት ዋና አስራ ስድስት ረዳት ዳኞች የሚመሩት የክለቦች ሻምፒዮና በነገው ዕለት በይፋ በሦስት ሜዳዎች በ10 ጨዋታዎች የሚጀመር ይሆናል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም

ምድብ ለ

አሊ ሀብቴ ጋራዠ ከ አሳይታ ወረዳ 3፡00
ዳንቦያ ከተማ ከ ወንዶ ገነት ከተማ 5፡00

ምድብ ሐ

ገንደ ሸበል ከ ሰመራ ሎጊያ 8፡00
አቃቂ ማዞሪያ ከ ቡሳ ከተማ 10፡00

በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ

ምድብ መ

ሀረር ዩናይትድ ከ ከቫርኔሎ ወረዳ 13 3፡00
አመያ ወረዳ ከ ቦንጋ መምህራን ኮልጅ 5፡00

ምድብ ሠ

አዲስ ቅዳም ከ ገንደ ተስፋ 8፡00
አለታ ወንዶ ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 10፡00

ደቡብ ኮሌጅ ሜዳ

ምድብ ረ
ቦሌ ክፍለ ከተማ ከ ድሬዳዋ ቀበሌ 06 3፡00
አማራ ሳይንት ከ ጋርዱላ 5፡00