ኤርትራን የሚገጥመው የዋልያው የመጀመርያ አሰላለፍ ታውቋል

ደረጃ ለመለየት የኤርትራ አቻውን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ አሰላለፍ ታውቋል።

ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን ከኤርትራ እና ቡሩንዲ ጋር አድርጎ ሁለት ነጥብ በማግኘት ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፍ የተሳነው የአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ስብስብ በሴካፋ ህግ መሠረት የደረጃ ጨዋታውን ከሰዓታት በኋላ ያከናውናል። በዚህ ጨዋታ ላይ የኤርትራ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን የሚፋለመው ዋልያው በጨዋታው የሚጠቀመው የመጀመሪያ አሰላለፍም ታውቋል።

በዚህም በውድድሩ ለሁለተኛ ጊዜ ኤርትራን የሚገጥመው የመጀመሪያ ስብስብ ውስጥ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከቡሩንዲው ጨዋታ ሦስት ለውጥ አድርገውበታል። በዚህም ኃይሌ ገብረትንሳኤ ወጥቶ አሥራት ቱንጆ፣ ሀብታሙ ተከስተ አርፎ በረከት ወልዴ እንዲሁም ዊልያም ሰለሞን ወጥቶ ወንድማገኝ ኃይሉ ወደ ሜዳ ገብተዋል።

የቡድኑ አሰላለፍ የሚከተለው ነው።

13 ፋሲል ገብረሚካኤል
3 ረመዳን የሱፍ
23 መሳይ ጳውሎስ
4 መናፍ ዐወል
21 አሥራት ቱንጆ
20 በረከት ወልዴ
14 ዳዊት ተፈራ
7 ወንድማገኝ ኃይሉ
17 ብሩክ በየነ
10 አቡበከር ናስር
22 ቸርነት ጉግሳ