ሀድያ ሆሳዕና የአምበሉን ውል አራዘመ

የግራ መስመር ተከላካዩ ሄኖክ አርፊጮ ለሁለት ተጨማሪ ዓመት በሀድያ ሆሳዕና ውሉን አራዝሟል፡፡

በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረት እየተመራ እስከ አሁን አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመው ሀድያ ሆሳዕና የአምበሉ ሄኖክ አርፊጮን ውል አድሷል፡፡ በሀድያ ሆሳዕና ረዘም ያለ ጊዜን ያሳለፈው እና ቡድኑንም በግራ ተከላካይነት እና በአምበልነት የመራው ተጫዋቹ በወላይታ ድቻን አምርቶ መጫወቱ ይታወሳል፡፡ ከሰሞኑ ወደ ሌላ ክለብ ያመራል ተብሎ ቢነገረም በነብሮቹ ቤት ሁለት ተጨማሪ ዓመታትን እንደሚያሳልፍ ተረጋግጧል፡፡