ሰበታ ከተማ ተጨማሪ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር በመግባት የነቃ ተሳትፎን እያደረጉ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን በሁለት ዓመት ውል በእጃቸው አስገብተዋል።

አራተኛ ፈራሚ ሆኖ ሰበታ የደረሰው ሳሙኤል ሳሊሶ ነው፡ በመከላከያ ጥሩ ጊዜያትን ካሳለፈ በኃላ 2011 መስከረም ወር ላይ ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቶ ከክለቡ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ በመጀመሪያ አመቱ ያሳካው ተጫዋቹ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ኮቪድ 19 ወደ ሀገራችን እስከሚገባ ድረስ በመቐለ ከቆየ በኃላ በሁለተኛው ዙር ወደ ወልቂጤ ያመራ ሲሆን የተጠናቀቀውን የ2013 የውድድር ዘመን ወደ ቀድሞ ክለቡ መከላከያ ተመልሶ ክለቡን ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲመለስ አስተዋፅኦ ካደረገ በኃላ በቀጣይ ዓመት ወደ በሰበታ መለያ ለመታየት አምርቷል፡፡

በዛሬው ዕለት መከላከያን የለቀቀ አራተኛ ሰበታን የተቀላቀለው አምስተኛ ፈራሚው በኃይሉ ግርማ ሆኗል። የቀድሞው የሙገር ሲሚንቶ የተከላካይ አማካይ ተጫዋች በመከላከያ ማለያ ያለፉትን አምስት የውድድር ዓመታት በአምበልነትም ጭምር የመራ ሲሆን በከፍተኛ ሊግ መከላከያን ወደ ፕሪምየር ሊጉ የመመለስ ስራን ከውኖ ማረፊያው በመከላከያ ያሰለጠኑት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ክለብ ሰበታ መሆኑ ዕርግጥ ሆኗል፡፡