ወላይታ ድቻ አራተኛ አዲስ ፈራሚውን አግኝቷል

ወላይታ ድቻ አመሻሹን የክረምቱ አራተኛ ፈራሚ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም መሪነት ሦስት አዳዲስ እና አምስት ነባር ተጫዋቾችን ያስፈረመው ወላይታ ድቻ በዛሬው ዕለት አማካዩ ሀብታሙ ንጉሤን አስፈርሟል፡፡ በጅማ አባጅፋር ጥሩ የውድድር ጊዜን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ያሳለፈው ባለ ተሰጥኦው አማካይ በክለቡ ለሁለት የውድድር ዘመናት የቆየ ሲሆን አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ተከትሎ ወደ ጦና ንቦቹ ቤት አምርቷል፡፡

ያጋሩ