አዳማ ከተማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ታደለ መንገሻ የአዳማ ከተማ አምስተኛ ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል።

በዝውውር ገበያው የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው አዳማ ከተማ ታደለ መንገሻን አምስተኛ ፈራሚው አድርጓል፡፡ በቴክኒክ ችሎታቸው ከሚጠቀሱት መሀል አንዱ የሆነው የቀድሞው የደደቢት፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አርባምንጭ ከተማ አማካይ ታደለ ከሁለት ዓመት በፊት ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በማምራት ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ከ2012 ጀምሮ በሰበታ ከተማ ሲጫወት ቆይቶ አሁን ደግሞ በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ለሚመራው አዳማ የሁለት ዓመት ፊርማውን አስፍሯል፡፡

ያጋሩ