ዩጋንዳዊው አማካይ ወደ ሀገሩ ተመልሷል

በሲዳማ ቡና የውድድር ዓመቱን ያሳለፈው አማካይ ወደ ሀገሩ የተመለሰበትን ዝውውር አጠናቋል።

ዩጋንዳዊው አይደክሜ የአማካይ መስመር ተጫዋች ያስር ሙገርዋ 2009 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበትን ዝውውር በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ማደረጉ አይዘነጋም። ተጫዋቹ አንድ ዓመት ለፈረሰኞቹ ግልጋሎግ ከሰጠ በኋላ ደግሞ ወደ ዐፄዎቹ ቤት አምርቶ ተጫውቷል። ከዛም ስሑል ሽረን ተቀላቅሎ ሲጫወት የነበረ ሲሆን በተተናቀቀው የውድድር ዘመን ደግሞ በሲዳማ ቡና መለያ በሊጉ ቆይታን አድርጓል።

ከደቂቃዎች በፊት በተሰማ መረጃ ደግሞ ተጫዋቹ ወደ ሀገሩ ዳግም በመመለስ ኬሲሲኤን መቀላቀሉ ተረጋግጧል። ተጫዋቹም እስከ 2023 ድረስ የሚያቆየውን ውል መፈረሙ ታውቋል።

ያጋሩ