ሰበታ ከተማ የወጣቱን ግብ ጠባቂ ውል አድሷል

ግብ ጠባቂው ሰለሞን ደምሴ በሰበታ ከተማ ውሉን አድሷል፡፡

በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው መሪነት አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ሰበታ ከተማ በዛሬው ዕለት የግብ ጠባቂው ሰለሞን ደምሴን ውል አራዝሟል፡፡ ከከፍተኛ ሊግ ጀምሮ ሰበታ ከተማን እያገለገለ የሚገኘው ሰለሞን አሁንም ለተጨማሪ ሦስት ዓመታት በሰበታ ለመቆየት ውሉን አድሷል፡፡

ያጋሩ