የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል የሚወጣበት ቀን ታውቋል

ኢትዮጵያን ተሳታፊ የሚያደርገው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል የሚወጣበት ቀን ተገልጿል።

በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ 2022 የተዘዋወረው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ በካሜሩን አስተናጋጅነት በጥር ወር እንደሚከናወን ይታወቃል። በውድድሩ የሚካፈሉ 24 ሀገራት ከተለዩ በኋላ የአህጉሪቱ የእግርኳስ የበላይ የሆነው ካፍ የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብሩ መቼ እንደሆነ የሚገልፅበት ቀን ሲጠበቅ ነበር።

ከደቂቃዎች በፊት ካፍ ባወጣው መረጃ መሠረት ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ የሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ነሐሴ 11 (ኦገስት 17) በካሜሩን ያውንዴ ኮንፈረንስ ሴንተር እንደሚወጣ ያመላክታል።

ያጋሩ