ሀድያ ሆሳዕና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አስፈረመ

የመስመር እና የፊት አጥቂው ሀብታሙ ታደሠ ወደ ሀድያ ሆሳዕና አምርቷል፡፡

በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት መሪነት እስከ አሁን አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመው ሀድያ ሆሳዕና ሀብታሙ ታደሠን አምስተኛ ፈራሚውን አድርጓል። በወልቂጤ ከተማ በከፍተኛ ሊጉ ሲጫወት ባሳየው መልካም እንቅስቃሴ መነሻነት በ2012 ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቶ የተጫወተው ሀብታሙ ሁለት ጥሩ የውድድር ዘመናትን በቡና ካሳለፈ በኋላ አሁን ወደ ሀድያ ሆሳዕና በሁለት ዓመት የውል ዕድሜ ማምራቱ ታውቋል።

ያጋሩ