ጅማ አባጅፋር የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሷል

በቅርቡ አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝነት የሾሙት ጅማ አባጅፋሮች በትናንትናው ዕለት ወደ ዝውውር ገበያው በመግባት ተጫዋቾች ሲያስፈርሙ የነባር ተጫዋቾችንም ውል አድሰዋል።

በትናንትናው ዕለት አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው ጅማ አባጅፋር የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት ከጋሻው ፕሮጀክት የተገኘው የመስመር ተከላካዩ ኢዳላሚን ናስር እና ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ቡድኑን የተቀላቀለው የመስመር አጥቂው ቤካም አብደላ ውላቸው ለሁለት ተጨማሪ ዓመት ተራዝሞላቸዋል።