የኢትዮጵያ እግርኳስ ድምፅ !
በኢትዮጵያ ቡና ሁለት የውድድር ዓመትን ያሳለፈው አቤል ከበደ ወደ ምስራቁ ክለብ ተጉዟል፡፡
ከዚህ ቀደም በመከላከያ በታዳጊ እና ዋናው ቡድን እንዲሁም ደግሞ በወልድያ የተጫወተው አቤል ከበደ ላለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በአሰልጣኝ ካሣዬ አራጌው ኢትዮጵያ ቡና አገልግሎት የሰጠ ሲሆን አሁን ደግሞ በሁለት ዓመት ውል ድሬዳዋን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡