በከፍተኛ ሊጉ ለአቃቂ ቃሊቲ ሲጫወት የነበረው የመስመር አጥቂ ለሰበታ ከተማ የሦስት ዓመት ውል ፈርሟል፡፡
በርካታ ዝውውሮች እንዲሁም የውል ማራዘም ሥራዎችን እየከወነ የሚገኘው ሰበታ ከተማ ዮናስ አቡሌን አስፈርሟል፡፡ ዘንድሮ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ በአቃቂ ቃሊቲ ቡድን ውስጥ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳየው ወጣቱ የመስመር ተጫዋች በበርካታ ክለቦች ዓይን ውስጥ ገብቶ የነበረ ሲሆን ማረፊያውን ሰበታ በማድረግ የሦስት ዓመት ውል ፈርሟል፡፡