የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አማኑኤል ጎበና ወደ ቀድሞ ክለቡ አዳማ ከተማ የተመለሰበትን ዝውውር ፈፅሟል።
ካለፈው ዓመት በተለየ መልኩ ኲዝውውሩ እየተሳፉ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች ስድስተኛ አዲስ ፈራሚያቸውን በእጃቸው አስገብተዋል፡፡አማኑኤል ጎበናም በሁለት ዓመት ውል አዲሱ የአዳማ ፈራሚ ሆኗል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስን በክለብ ደረጃ የጀመረው አይደክሜው አማካዬ በክለቡ ረዘም ያለ ጊዜ አሳልፎ ወደ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አምርቶ መጫወት የቻለ ሲሆን 2011 ላይ ወደ አዳማ ከተማ በማምራት ቆይታ አድርጎ በመቀጠል የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በሀድያ ሆሳዕና ከቀድሞው አሰልጣኙ አሸናፊ በቀለ ጋር አሳልፎ ከአንድ የውድድር ዓመት በኃላ ዳግም አዳማን ተቀላቅሏል፡፡