ከሳምንት በፊት ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ የአራት ነባር ተጫዋቾችን ውል ያደሰው መከላከያ የመስመር አጥቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
ኤርሚያስ ኃይሉን የክለቡ አራተኛ አዲስ ፈራሚ ተጫዋች ነው፡ የቀድሞው የኒያላ፣ ዳሽን ቢራ፣ ፋሲል ከነማ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር የመስመር አጥቂ ጅማን ከለቀቀ በኋላ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በመጫወት አሳልፏል፡፡ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎም ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚመልሰውን ዝውውር አድርጓል።
ጦሩ ከዚህ ቀደም ሙሴ ገብረኪዳን፣ ዳዊት ወርቁ እና ልደቱ ጌታቸውን ሲያስፈርም የዳዊት ማሞ፣ አሌክስ ተሰማ፣ ጃፋር ደሊል እና ገናናው ረጋሳን ውል ማደሱ የሚታወስ ነው።