አርባምንጭ ከተማ የመስመር ተጫዋች አስፈረመ

ሱራፌል ዳንኤል አዞዎቹን ተቀላቅሏል፡፡

የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ውል ካራዘመ በኋላ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመው እና የበርካቶቹን ውልም ያደሰው አርባምንጭ ከተማ የመስመር አጥቂው ሱራፌል ዳንኤልን የክለቡ አራተኛ አዲስ ፈራሚ ማድረግ ችሏል። የቀድሞው የድሬዳዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ሀድያ ሆሳዕናን ከለቀቀ በኃላ በከፍተኛ ሊጉ መከላከያ ዓመቱን አሳልፎ በአንድ ዓመት ውል መቀላቀሉ ዕርግጥ ሆኗል፡፡

ያጋሩ