ወላይታ ድቻ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አስፈረመ

ከሰዓታት በፊት ግብ ጠባቂ አስፈርመው የነበሩት ወላይታ ድቻዎች የአጥቂ መስመር ተጫዋችን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል ፡፡

ቃልኪዳን ዘላለም ወላይታ ድቻን በሁለት ዓመት ውል የተቀላቀለው ተጫዋች ነው። በኢትዮጵያ ቡና ከወጣት ቡድኑ አድጎ በዋናው ቡድን መጫወት የቻለው ቃልኪዳን በመቀጠል በደደቢት የተጫወተ ሲሆን የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በሰበታ ከተማ በመጫወት አሳልፏል።

በመሐል እና መስመር አጥቂነት መጫወት የሚችለው ቃልኪዳን የፀጋዬ ኪዳነማርያምን ቡድን የተቀላቀለ ዘጠነኛው አዲስ ፈራሚ ሆኗል።

👆 በዛሬው ዕለት ቡድኑን የተቀላቀለው ግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድ

ያጋሩ