ወላይታ ድቻ የአምበሉን ውል አደሰ

ወላይታ ድቻዎች የአምበላቸው ደጉ ደበበን ውል አድሰዋል፡፡

እግር ኳስን በአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ከጀመረ በኋላ ረጅሙን የእግር ኳስ ጊዜውን በቅዱስ ጊዮርጊስ በመሐል ተከላካይነት እና በአምበልነት ያሳለፈው እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ስኬታማ ጊዜ የነበረው ደጉ ደበበ ፈረሰኞቹን ከለቀቀ በኃላ ከ2011 አጋማሽ ጀምሮ በወላይታ ድቻ እያሳለፈ ይገኝ የነበረ ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ከእግር ኳስ ተጫዋችነቱ ይገለላል ወይስ ይቀጥላል የሚለው አነጋጋሪ የነበረ ቢሆንም ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ “የመጫወት አቅሙ አለኝ” በማለት በቀጣይም የመጫወት ዝግጁነቱን መግለፁ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ለተጨማሪ አንድ ዓመት በጦና ንቦቹ ቤት ለመቆየት ውሉን አድሷል፡፡

ያጋሩ