ጋናዊው አጥቂ ዝውውሩን አጠናቋል

አጥቂው ኦሴ ማውሊ በይፋ የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች ሆኗል፡፡

ከቀናት በፊት ወደ ባህር ዳር ለማምራት ከስምምነት ደርሶ የነበረው እሴ ማውሊ ዛሬ አመሻሽ ዝውውሩን ማጠናቀቁ ይፋ ተደርጓል። ጋናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ከኢትዮጵያ እግር ኳስ የተዋወቀው በ2011 መቐለ 70 እንደርታ በመጫወት ሲሆን በመቀጠል ለፋሲል ከነማም ግልጋሎት ሰጥቷል፡፡ ወደ ሀገሩ ተመልሶ እስከ ዓመቱ አጋማሽ ካሳለፈ በኃላ በመጋቢት ወር ወደ ሰበታ አምርቶ የስድስት ወራት ቆይታ ያደረገው ማውሊ በሰበታ ድንቅ ጊዜ ማሳለፍ ችሏል።

የመስመር እና የመሐል አጥቂ ሆኖ መጫወት የሚችለው ማውሊ በሰበታ ካሰለጠኑት አብረሀም መብራቱ ጋር በባህር ዳር የሚገናኝ ሲሆን ምንይሉ ወንድሙ እና ባዬ ገዛኸኝን በለቀቀው ቡድን ዋነኛ የፊት መስመር ተሰላፊ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡