ማሊያዊው አጥቂ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አምርቷል

በዛሬው ዕለት መሳይ ጳውሎስን ያስፈረመው ድሬዳዋ ከተማ ማሊያዊውን አጥቂ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን ውል ካደሰ በኃላ ጋዲሳ መብራቴ፣ እንየው ካሣሁን እና ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ መሳይ ጳውሎስን ያስፈረመው ድሬዳዋ ከተማ ማሊያዊው አጥቂ ማማዱ ሲዲቤን በሁለት ዓመት ውል አስፈርሟል። በ2011 ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኃላ በጅማ አባጅፋር በመጫወት ከሀገራችን እግር ኳስ ጋር የተዋወቀው አጥቂው በመቀጠል በተሰረዘው የ2012 የውድድር ዓመት በባህር ዳር፣ የተጠናቀቀውን የዝድድር ዓመት ደግሞ ለሲዳማ በመጫወት አሳልፏል፡፡

ድሬዳዋ ከተማ ከአዳዲስ ፈራሚዎቹ ባሻገር የሦስት ነባር ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙ አይዘነጋም፡፡