የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ቅዳሜ ይደረጋሉ

የምድብ ጨዋታዎቹን ያገባደደው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ወደ አንደኛ ሊግ የሚገቡ ቡድኖችን ለመለየት ቅዳሜ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይደረግበታል።

የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀው ወደ አስራ ስድስት ውስጥ የገቡ ክለቦችን በትናንትናው ዕለት መለየቱ ይታወሳል፡፡ አስራ አንድ ምድቦችን ይዞ የተካሄደው ይህ ውድድር ከየምደቡ አንደኛ የሆኑ ክለቦች በቀጥታ በማለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን ቀድመው ያወቁ ሲሆን ጥሩ ሁለተኛ በመሆን የማለፍ ዕድልን ያገኙት ዱከም ከተማ፣ ጋምቤላ አብይ አካዳሚ እና ሊሙገነት ከተማ ዛሬ ረፋድ በሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል በተደረገ ድልድል ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል፡፡

ቅዳሜ ነሐሴ 1 በሁለት ሜዳዎች ስምንት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን አሸናፊ ቡድኖች በቀጥታ ወደ 2014 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ተሸናፊ የሆኑ ቀሪ ስምንት ክለቦች እርስ በእርስ በሚያደርጉት ጨዋታ መሠረት የሚያሸንፉት አራቱ ክለቦችን ጨምሮ በድምሩ 12 ክለቦች ማደጋቸውን የሚያረጋግጡ ይሆናል፡፡

የጥሎማለፍ መርሐ ግብር

በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም

ቡሬ ዳሞት ከ ዱከም ከተማ 2፡00
ቡሳ ከተማ ከ ቦዲቲ ከተማ 4፡00
ኑዌር ዞን ከ ጋምቤላ አብይ አካዳሚ 7፡00
ቫርኔሮ ወረዳ 13 ከ ወንዶ ገነት ወረዳ 9፡00

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም

አዲስ ቅዳም ከ ካማሺ ከተማ 2፡00
ቦሌ ክፍለከተማ ከ ምህረት ክለብ 4፡00
ምስራቅ ክፍለከተማ ከ ካራማራ 7፡00
ዱራሜ ከተማ ከ ሊሙገነት ከተማ 9፡00