ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ድሬዳዋ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈረመ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተሳታፊው ድሬዳዋ ከተማ የመስመር ተከላካይ አስፈርሟል፡፡

በርካታ ተጫዋቾች ወደተለያዩ ክለቦች ያመሩበት የአሰልጣኝ ብዙዓየሁ ጀምበሩ ቡድን ድሬዳዋ ከተማ እንደ አዲስ ክለቡን እየገነባ የሚገኝ ሲሆን ትዕግስት ዳዊትን ዘጠነኛ ፈራሚው አድርጓል፡፡በሀዋሳ ከተማ የክለብ የእግር ኳስ ህይወቷን በ2004 የጀመረችሁ የመስመር ተከላካይዋ ሀዋሳን ከለቀቀች በኋላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በመከላከያ በመጫወት አሳልፋለች፡፡በጦሩ ቤት ውሏ ያበቃው ተጫዋቿ ማረፊያዋ የምስራቁ ክለብ ድሬዳዋ ሆኗል፡፡