ረፋድ በተደረጉ ጨዋታዎች አራት ቡድኖች ወደ አንደኛ ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል

በኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ረፋድ በተደረጉ ጨዋታዎች አራት ክለቦች ወደ አንደኛ ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ላይ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። ቀደም ብል ጠዋት 2፡00 ሲል የአማራ ክልሉ ቡሬ ዳሞት ከኦሮሚያው ዱከም ከተማ ተገናኝተው ዱከም ከተማዎች 1ለ0 ረተው ወደ አንደኛ ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ቀጥሎ 4፡00 ሲል ቡሳ ከተማ እና ቦዲቲ ከተማን ያገናኘው ጨዋታው መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 ተጠናቆ በተሰጠ የመለያ ምት የኦሮሚያው ቡሳ ከተማ 5ለ4 በማሸነፍ ወደ 2014 የአንደኛ ሊግ የተሳትፎ ትኬቱን ቆርጧል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየምም በተመሳሳይ ሁለት ጨዋታዎች ተከናውኗዋል፡፡ 2፡00 ሲል በውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የቻሉትን አዲስ ቅዳም እና ካማሺ ከተማ ተገናኝተው የቤንሻንጉል ጉሙዙ ካማሺ 1ለ0 አሸናፊ በመሆናቸው ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ 4፡00 ሲል በዚሁ ሜዳ ሁለቱ የአዲስ አበባ ክለቦች የሆኑት ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ምኅረት ክለብን ያገናኘው መርሀግብር 2ለ2 ጨዋታው ተጠናቆ በተሰጠ የመለያ ምት ቦሌ ክፍለ ከተማ 5ለ4 ረትቶ አድጓል፡፡

ሌሎች አራት ክለቦች የሚለየው ጨዋታ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እየተደረገ ይገኛል።

ሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ

ኑዌር ዞን ከ ጋምቤላ አብይ አካዳሚ 7፡00
ቫርኔሮ ወረዳ 13 ከ ወንዶ ገነት 9፡00

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ

ምስራቅ ክፍለከተማ ከ ካራማራ ክለብ 7፡00
ዱራሜ ከተማ ከ ሊሙ ገነት ከተማ 9፡00

*የተሸናፉ ቡድኗች ተጨማሪ ዕድል ያላቸው ሲሆን እርስ በእርስ ተገናኝተው አሸናፊ የሆኑ አራት ክለቦች በቀጣይ አዳጊ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

ያጋሩ