የኢትዮጵያ ቡና ሥራ አመራር ቦርድ በአሰልጣኝ ካሣዬን ዙርያ አቅጣጫ ማስቀመጡ ታውቋል።
የወቅቱ መነጋገሪያ ርዕስ የሆነው የአሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ ወደ ሥራ ገበታው አለመግባት እና የምክትል አሰልጣኙን በተመለከተ ውል አላራዝምም ባለው ክለቡ መካከል ውዝግብ መፈጠሩን በተለያዩ ዘገባችን መግለፃችን ይታወቃል።
ትናንት ማምሻውን የተፈጠረውን ሁኔታ ዕልባት ለመስጠት ስብሰባ እንዳደረገ የተነገረው የክለቡ ቦርድ ምን ውሳኔ እንደወሰነ የክለቡን ከፍተኛ አመራር መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞን ሀሳብ ይዘን እንደምንቀርብ መግለፃችን ይታወቃል። ሆኖም መቶ አለቃፍቃደ ማሞ በተደራራቢ ሥራ ምክንያት በዚህ ዘገባችን ሀሳባቸውን ማካተት አልቻልንም። ያም ቢሆን ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የክለቡ አመራር ባገኘነው መረጃ አሰልጣኝ ካሣዬ ከሁሉም በፊት ወደ ሥራ ገበታው መመለስ እንዳለበት፣ ሥራ እየተበደለ ለጥያቄው መልስ መስጠት ክለቡ እንደሚቸገር እና ክለቡ አሰልጣኝ ካሣዬ ላቀረበው ማንኛውም ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ በሒደት እንደሚወስን አቅጣጫ መሰጠቱን ሰምተናል።