በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በባቱ ከተማ ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 3 ድረስ የሚካሄደው ከ17 ዓመት በታች ውድድር የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።
በአስር የፕሪምየር ሊግ ክለቦች እና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች እና በስምንት ክልል በጥቅሉ 20 ቡድኖች የሚካፈሉበት የምድብ ድልድሉ ይሄን ይመስላል።
በምድብ ሀ
አዳማ ከተማ
ኦሮምያ ክልል
አዲስ አበበ ከተማ
ጋምቤላ ክልል
ምድብ ለ
ሀዋሳ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ
ሐረሪ ክልል
ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ምድብ ሐ
ሲዳማ ክልል
ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሱማሌ ክልል
ወላይታ ድቻ
ምድብ መ
አማራ ክልል
ሰበታ ከተማ
ወልቂጤ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር
ምድብ ሠ
ኢትዮጵያ ቡና
አፋር ክልል
ደቡብ ክልል
ባህር ዳር ከተማ
በአምስት ምድብ ተከፍሎ በሚካሄደው ውድድር ከየምድባቸው አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ አስር ቡድኖች በቀጥታ የሚያልፉ ሲሆን ጥሩ ሦስተኛ የሆኑ ስድስት ቡድኖች ተካተው በአስራ ስድስት ቡድኖች መካከል ጥሎ ማለፍ በማድረግ ወደ ቀጣዩ ወደ ሩብ ፍፃሜ የሚያመሩ ቡድኖች የሚለይ ይሆናል።
በዚህ ውድድር እንደሚሳተፋሉ የተጠበቁት ፋሲል ከነማ፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ ሀድያ ሆሳዕና፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና እና መከላከያ እንደማይኖሩ ተረጋግጧል።
በጁፒተር ሆቴል የተካሄደውን አጠቃለይ የስብሰባ ሒደት ከቆይታ በኃላ በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል።