ሲዳማ ቡና ከአማካዩ ጋር ተለያየ

ሲዳማ ቡና ከአምስት ዓመታት በላይ በአማካይነት ካገለገለው ተጫዋች ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

ዮሴፍ ዮሐንስ ከክለቡ ጋር የተለያየው ተጫዋች ነው፡፡ ከሀዋሳ ከተማ የተስፋ ቡድን ከተገኘ በኃላ በሀላባ ከተማ ከተጫወተ በኋላ ወደ ሲዳማ ቡና የመጣው ዮሴፍ በቀጣዩ ዓመት በክለቡ የሚያቆየው የአንድ ዓመት የውል ጊዜ የነበረው ቢሆንም በስምምነት ተለያይቷል፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ መሠረት ከክለቡ ጋር የተለያየው ተጫዋቹ ቅድመ ስምምነቶችን ከሌላ የፕሪምየር ሊግ ቡድን ጋር ያደረገ ሲሆን በጥቂት ቀናቶች ውስጥ አዲሱ ክለቡን በሁለት ዓመት ውል እንደሚቀላቀልም አረጋግጠናል፡፡

ያጋሩ