ጅማ አባጅፋር የመሐል ተከላካይ አስፈርሟል

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የነበረው የመሐል ተከላካይ መዳረሻው ጅማ ሆኗል።

አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለን ከሾሙ በኋላ ዘንድሮ ካሳለፉት መሳቀቅ የተሞላበት የውድድር ዓመት ተጠናክሮ ለመምጣት እንቅስቃሴ የጀመሩት ጅማ አባጅፋሮች ወጣት እና አንጋፋ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው እየቀላቀሉ ይገኛሉ። ከደቂቃዎች በፊት በተገኘ መረጃ ደግሞ ክለቡ በአዲስ አበባ ከተማ የውድድር ዓመቱን ያሳለፈው እና በሴካፋ ውድድር በተካፈለው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የነበረው የመሐል ተከላካይ ኢያሱ ለገሠን ማስፈረሙ ታውቋል።