ባህር ዳር ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

በርካታ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሰነበተው ባህር ዳር ከተማ የክረምቱ ሦስተኛ አዲስ ግብ ጠባቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ መሪነት በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እየቀላቀለ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ ከፋሲል ገብረሚካኤል እና አቡበከር ኑሪ ቀጥሎ ሦስተኛ አዲስ ግብ ጠባቂን በሁለት አመት ውል አስፈርሟል፡፡ ይገርማል መኳንንት ክለቡን የተቀላቀለው አዲሱ ተጫዋች ሆኗል፡፡ ከባህር ዳር አካባቢ የተገኘው እና በአማራ ውሀ ሥራዎች (አውሥኮድ) የክለብ ህይወትን የጀመረው ይህ ግብ ጠባቂ በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ኢኮስኮ ደግሞ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት በመጫወት አሳልፏል፡፡