
“ለከነማዬ እሮጣለው” በሚል መሪ ቃል ለአርባምንጭ ከተማ ክለብ የገቢ ማስገኛ ሩጫ ዛሬ ተካሄደ
የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብን በገቢ ለማጠናከር የተለያዩ የገቢ ማስገኛ መርሀግብሮች እየተደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ “ለክለቤ እሮጣለሁ” በሚል ስያሜ በከተማዋ ሩጫ ተካሂዷል፡፡
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ጉልህ ድርሻ ካላቸው አካባቢዎች መሐል አርባምንጭ አንዱ ነው፡፡በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከዚህ ቀደም ተሳታፊ የነበረው እና ወደ ከፍተኛ ሊጉ ወርዶ በድጋሚ ከሦስት ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ የተመለሰው አርባምንጭ ከተማ በፕሪምየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆን እና በድጋሚ የመውረድ ስጋት እንዳይገጥመው በገቢ መጠናከር ይኖርበታል በማለት ክለቡ ራሱን በፋይናንስ ከሰሞኑ ማጠናከር ላይ ተጠምዷል፡፡ ከቀናቶች በፊት በአርባምንጭ እና አካባቢ የሚገኙ ባለሀብቶችን በማስተባበር የገቢ ማስገኛ የእራት መርሀግብር ያከናወነ ሲሆን በዛሬው ዕለት ቅዳሜ ጠዋት ደግሞ በርካታ የክለቡ ደጋፊዎች፣ የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ፣ ተጫዋቾች፣ የክለቡ ወዳጆች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት አካላት እና ሌሎችም ጭምር የተሳተፉበትን “ለከነማዬ እሮጣለው” በሚል ስያሜ የሩጫ መርሀግብርን አካሂዷል፡፡
የሩጫ መርሀግብሩ ከተጠናቀቀ በኋላ የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳደሪ እና የክለቡ የበላይ ጠበቂ አቶ ብርሀኑ ዘውዴ ክለቡን ለመደገፍ ሁሉም አካላት ተሳትፎ ማድረግ በመቻላቸው ምስጋናን ያቀረቡ ሲሆን የክለቡ ፕሬዝዳንት እና የከተማው ከንቲባ ሰብስቤ ቡናቤ በበኩላቸው በተመሳሳይ ለተሳታፊዎች ምስጋናን አቅርበው ልክ በሩጫው የታየውን ርብርብ በተለያዩ ወቅቶች ከክለቡ ጎን በመሆን እንዲደግሙት በንግግራቸው ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም በሩጫው ተሳትፈው ከአንድ እስከ ሦስት በሁለቱም ፆታ ለወጡት የተለያዩ ሽልማቶች ተሰጥቶ ሥነ ስርዓቱ ተጠናቋል፡፡
ተዛማጅ ፅሁፎች
የሉሲዎቹ ዋና አሰልጣኝ ተጫዋቾችን ጠርተዋል
በዩጋንዳ ለሚደረገው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ23 ተጫዋቾችን ጥሪ አድርሷል፡፡ በዩጋንዳ ከግንቦት 24 ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ለሚደረገው...
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ተራዘመ
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር የሚጀመርበት ቀን ተገፍቷል፡፡ የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች በሀዋሳ ጅምራቸውን አድርገው...
የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ተራዘመ
በዩጋንዳ አስተናጋጅነት የሚዘጋጀው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የቀን ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ ሉሲዎቹን ተሳታፊ የሚያደርገው የዘንድሮው የሴካፋ የሴቶች ዋንጫ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡...
“በእያንዳንዱ ጨዋታ የሚሰጠኝን ዕድል መጠቀም ላይ ነው እያተኮርኩ ያለሁት” ዳግም ተፈራ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ እየታዩ ካሉ ጥሩ ግብ ጠባቂዎች መካከል አንዱ ከሆነው ወጣት ጋር ቆይታ አድርገናል። የ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ...
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል
ከረፋድ አንስቶ ካዛንቺስ በሚገኘው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የዋለው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ...
ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት የዛሬ ጨዋታዎች ውሎ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት የመጀመርያ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ሀዋሳ ከተማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዲያ...