ሲዳማ ቡና የአጥቂውን ውል አድሷል

ከሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን የተገኘው አጥቂ ውሉን አራዝሟል፡፡

ይገዙ ቦጋለ ውሉ ለሁለት ተጨማሪ ዓመት የተራዘመ ተጫዋች ነው፡፡ ከሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን የተገኘውና አቅሙን እያሳየ የሚገኘው አጥቂው ያለፉትን አምስት የውድድር ዘመናት ለዋናው ቡድን አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ጅማሮ ከገጠመው ጉዳት ካገገመ በኋላ ሲዳማ ቡና የመውረድ ስጋት በነበረበት ወቅት በመጨረሻዎቹ የሊጉ ሳምንታት ወደ ሜዳ በመመለስ ክለቡን ከታደጉ ተጫዋቾች መሐል አንዱ የሆነው ይገዙ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በክለቡ ተጨማሪ ዓመታትን ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል፡፡

ያጋሩ