ተጨማሪ ተጫዋች ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቅሏል

አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከቸርነት ጉግሳ በተጨማሪ ሌላ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ከያዝነው ወር መገባደጃ ጀምሮ ያከናውናል። ብሔራዊ ቡድኑ ከጋና እና ዚምባብዌ ጋር ላለበት ጨዋታ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ ቢያቀርብም አራት ተጫዋቾች (ሙጂብ፣ ሀይደር፣ አቡበከር እና ፍፁም) በቋሚና ጊዜያዊነት ስብስቡን ሳይቀላቀሉ ቀርተዋል። ይህንን ተከትሎም አሠልጣኙ የቅዱስ ጊዮርጊሱን የመስመር አጥቂ ቸርነት ጉግሳን መጥራታቸውን ቀድመን የዘገብን ሲሆን አሁን በተገኘ መረጃ ደግሞ የፋሲል ከነማው አማካይ በዛብህ መለዮ ስብስቡን እንዲቀላቀል ጥሪ እንደደረሰው አውቀናል።

በዛብህ የሀይደር ሸረፋን ሙሉ ለሙሉ ከቡድኑ መውጣትን ተከትሎም በአማካይ መስመር ላይ መሳሳት እንዳይኖር ጥሪ እንደደረሰው ተረድተናል። ተጫዋቹም በዛሬው ዕለት አዳማ መድረሱን እና ቡድኑን መቀላቀሉን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።