የግብ ጠባቂው ጉዳይ መፍትሔ አግኝቷል

በድሬዳዋ ከተማ የሚያቆየው ቀሪ ኮንትራት አለው በማለት ወደ ወላይታ ድቻ የሚያደርገው ዝውውር ዕንከን ገጥሞት የቆየው ጉዳይ መፍትሔ አግኝቷል።

በቅርቡ በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ስብሰብ ለሁለት ዓመት ውል የተቀላቀለው ግብጠባቂው ወንደሰን አሸናፊ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ያገኘው አጋጣሚ ላይ ጥያቄ ተነስቶ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ከዘንድሮ ከግማሽ ዓመት ጀምሮ የተጫወተበት ድሬዳዋ ከተማ ” የትም መሄድ አይችልም ከእኛ ጋር የሚያቆየው ኮንትራት አለው” በማለቱ ነበር። ሆኖም ክለቡ ዛሬ በላከው ደብዳቤ ኮንትራቱ ሰኔ 30 ያለቀ መሆኑን በፃፉት የመልቀቂያ ደብዳቤ አረጋግጠዋል። በዚህም መሰረት ወንደሰን አሸናፊ ወደ ቀድሞ ክለቡ ወላይታ ድቻ ያደረገው ዝውውር እርግጥ ሆኗል።

ያጋሩ