ወላይታ ድቻ ስምንት ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል

ከሰሞኑ በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም አማካኝነት ከ20 ዓመት ቡድኑ ምልመላን ሲያከናውን የነበረው ወላይታ ድቻ ስምንት ወጣቶችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል፡፡

በርካታ ተጫዋቾችን ያስፈረመውና በዛው መጠን ከበርካታ ተጫዋቾች ጋር የተለያየው ወላይታ ድቻ አሁን ደግሞ በአሰልጣኝ ተመስገን ሎሀ ከሚመራው እና በ2013 ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግን እየመራ በበጀት የተነሳ ውድድሩን ካቋረጠው የክለቡ ከ20 ዓመት ቡድን አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ከሰሞኑ ምልመላን ሲያደርጉ ሰንብተው በመጨረሻም ስምንት ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን እንዲያድጉ አድርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት አብነት ይስሀቅ (ግብጠባቂ)፣ ዮናታን ኤልያስ (ተከላካይ)፣ አዛርያስ አቤል (ተከላካይ)፣ ቢኒያም አበበ (ተከላካይ)፣ ኬኔዲ ከበደ (ተከላካይ)፣ ውብሸት ወልዴ (አማካይ)፣ ዘላለም አባተ (አማካይ) እና ሳሙኤል ጃጊሶ (አማካይ) ማደጋቸው የተረጋገጡ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

ካደጉት መካከል ግብ ጠባቂው አብነት ይስሀቅ ቡድኑ በርካታ ተጫዋቾች በኮቪድ በተጠቁበት ወቅት ከሀዋሳ ከተማ ጋር በተደረገው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በተጫዋችነት መሰለፉ የሚታወስ ሲሆን አዛርያ አቤል በዋናው ቡድን በርካታ ጨዋታዎች ላይ ተጠባባቂ እንደነበር ይታወሳል።