ሀድያ ሆሳዕና የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረትን በዋና አሰልጣኝ መንበር የሾመው ሀድያ ሆሳዕና የ2014 የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምርበት ቀን ተገልጿል፡፡

ለሁለት ዓመታት በሚቆይ የውል ዕድሜ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረትን ከቀጠረ በኋላ የተለያዩ ተጫዋቾችን ከፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሲያስፈርም የቆየው ክለቡ በቀጣዮቹ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደሚቀላቅል እና ከ20 ዓመት ቡድኑም ወጣቶች እንደሚያሳድግ የሚጠበቅ ሲሆን ለ2014 የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የፊታችን ሰኞ ነሐሴ 17 ጀምሮ ለመጀመር እቅድ መያዙን አሰልጣኙ ሙሉጌታ ገልፀውልናል፡፡

የክለቡ ተጫዋቾች ነሐሴ 17 በመሰባሰብ በ18 እና በ19 የቅድመ ምርመራ እና የኮቪድ 19 ምርመራ በመከወን ነሐሴ 20 የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በሆሳዕና ከተማ አልያም ደግሞ ሀዋሳ ላይ ሊያደርግ እንደተዘጋጀ ሰምተናል፡፡