ፕሪሚየር ሊግ ፡ ወላይታ ድቻ እና መከላከያ ወደ ድል ሲመለሱ ባንክ 2-0 ከመመራት ተነስቶ ነጥብ ተጋርቷል 

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛው ዙር ማሳረግያ ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገው ወላይታ ድቻ እና መከላከያ ወደ ድል ተመልሰዋል፡፡ ንግድ ባንክ ደግሞ በኤሌክትሪክ 2-0 ከመመራት ተነስቶ አቻ ተለያይቷል፡፡

ቦዲቲ ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ በመጨረሻ ደቂ በተገኘች ግብ 2-1 አሸንፎ ደረጃውን ወደ 4ኛነት ከፍ አድርጓል፡፡

ድቻዎች በ6ኛው ደቂቃ በበዛብህ መለዮ አማካኝነት ቀዳሚ መሆን ሲችሉ አብዱልከሪም መሃመድ ባለፈው ሳምንት ሀዲያ ሆሳዕና ላይ ካስቆጠረው ጋር የሚመሳሰል ግብ በ13ኛው ደቂቃ አስቆጥሮ ቡናን አቻ አድርጓል፡፡ የጨዋታው የመጀርመያ አጋማሽም ተጨማሪ ጎል እንዲሁም እምብዛም የግብ ሙከራ ሳያስተናግድ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ከእረፍት መልስ በተለይም በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ጫና ፈጥረው በመጫወት ወላይታ ድቻዎች የተሻሉ የነበሩ ሲሆን 90 ደቂው ተጠናቆ በጭማሪው ደቂቃ ላይ አርቢቴር ይርጋለም ወልደጊዮርጊስ የፍጹም ቅታት ምት አላግባብ ከልክለዋል በሚል የድቻ ደጋፊዎች ድንጋይ ወደ ሜዳ መወርወር በመጀራቸው ጨዋታው ለ10 ደቂዎች ያህል ለመቋረጥ ተገዷል፡፡ ግርግሩ ከተረጋጋ በኋላ የተቋረጠው ጨዋታ በድጋሚ ተጀምሮ ወደ ቡና የግብ ክልል የተላከው ኳስ በሃሪሰን እና ኤፍሬም አለመግባባት ኤፍሬም በግንባሩ ገጭቶ በቡና መረብ ላይ አሳርፎታል፡፡ ጨዋታውም በድቻ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ውጤቱ ወላይታ ድቻን በ20 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲያስቀምጠው ኢትዮጵያ ቡና 2 ደረጃ በመውረድ 11ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡

IMG_0165

በተመሳሳይ 9 ሰአት አዲስ አበባ ስታድየም ላይ አዳማ ከተማን ያስተናገደው መከላከያ 1-0 በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሷል፡፡ በ15ኛው ደቂቃ ጃኮብ ፔንዛ መሃመድ ናስርን በመጥለፉ መከላከያ የፍጹም ቅጣት ምት ቢያገኝም መሃመድ ናስር መትቶ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ተመልሶበታል፡፡ ከፍፁምቀ ታት ምቱ መሳት በኋላም የተሸለ መንቀሳቀስ የቻሉት መከላከያዎች ሲሆኑ በ32ኛው ደቂቃ በጥሩ ቅብብል ተመስርቶ የመጣውን ኳስ መሃመድ ለቴዎድሮስ አቀብሎት የግራ መስመር ተከላካዩ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አሳርፏታል፡፡

ሁለተኛው አጋማሽ እምብዛም ማራኪ እቅስቃሴ ያልታየበት ሲሆን ከ75ኛው ደቂቃ በኋላ አዳማ ከተማዎች የአቻነት ግብ ለማግኘት ጫና መፍጠር ችለው ነበር፡፡ በርካታ የማእዘን ምቶችን አግኝተው የነበረ ቢሆንም ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ቋሚ አሰላለፍ የተመለሰው ጀማል ጣሰውን መረብ ሳደፍሩ ጨዋታው ተጠናቋል፡፡ ቡናቸውን ለመደገፍ ከአዳማ የመጡት ደጋፊዎችም በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ላይ የተቃውሞ ድምጽ ሲያሰሙ ተስተውሏል፡፡

ውጤቱ አዳማ ከተማን ለ3ኛ ተከታታይ ሽንፈት ዳርጎት በነበረበት 3ኛ ደረጃ እንዲረጋ ሲያደረገው ሁለት ጨዋታ የሚቀረው መከላከያ የወራጅ ቀጠናውን ለዳሽን ቢራ አስረክቦ ደረጃውን እንዲያሻሽል አድርጎታል፡፡

11፡30 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ 2-2 ተፈፅሟል፡፡ ኤሌክትሪክም የ2-0 መሪነቱ ማስጠበቅ ሳይችል ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል፡፡ በድንቅ አቋም ላ የሚገኘው ፒትር ኑዋድኬ የፌቮ ኢማኑኤል ከግብ ክልሉ ለቆ መውጣት ተመልክቶ በግሩም ሁኔታ ባስቆጠራት ግብ ኤሌክትሪክ መምራት የጀመረው ገና በ3ኛው ደቂቃ ነበር፡፡ ከ7 ደቂዎች በኋላ አወት ገ/ሚካኤል ከቀኝ መስመር በጥሩ ሁኔታ ያሻገረለትን ኳስ ፍጹም ገብረማርያም በድንቅ አጨራረስ ቀያዮቹ 2-0 እንዲመሩ አስችሎ ነበር፡፡ በ29ኛው ደቂ ተስፋዬ መላኩ በሰለሞን ገብረመህን ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ኤፍሬም አሻሞ በቀላሉ አስቆጥሮ ባንክን ወደ ጨዋታው የመለሰ ሲሆን ኤሌክትሪኮች የፍፁም ቅጣት ምቱ አላግባብ ተሰጥቶብናል በሚል ክስ አስመዝግበዋል፡፡ ፈጣን ፣ እልህ የተቀላቀለበት እና የግብ ሙከራዎች ያስተናገደው የመጀመርያ አጋማሽ  የተጠናቀቀውም በኤሌክትሪክ 2-1 መሪነት ነበር፡፡

በ2ኛው አጋማሽ ንግድ ባንኮች የተሸለ መንቀሳቀስ የቻሉ ሲሆን በ49ኛው ደቂቃ ኤፍሬም አሻሞ በራሱ ጥረት ያገኘውን ኳስ ተጠቅሞ ንግድ ባንክን አቻ አድርጓል፡፡ ፒተር ኑዋድኬ የመታውን የቅጣት ምት ፌቮ በአስደናቂ ሁኔታ ያወጣበት ፣ ጋብሬል አህመድ ከርቀት አክርሮ የመታውን ግሩም ኳስ አሰግድ በአስደናቂ ቅልጥፍና ያወጣበት ሙከራዎች በሁለተኛው አጋማሽ ከታዩ ሙከራዎች ዋንኞቹ ነበሩ፡፡

የሊጉ መደበኛ የአንደኛ ዙር ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን መከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታቸውን በመጋቢት እና ሚያዝያ ወራት ያደርጋሉ፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

shfiy

ከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ

zmjfdb

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *