የጣና ሞገዶቹ ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን የሾሙት ባህር ዳር ከተማዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት 33 ነጥቦችን በመያዝ 7ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ባህር ዳር ከተማ በ2014 የሊጉ ውድድር ተጠናክሮ ለመቅረብ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። በቅድሚያ ከአሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን ጋር በመስማማት በይፋ ወደ እንቅስቃሴ የገባው ክለቡም ከዛ ፊቱን ወደ ተጫዋቾች ዝውውር በማዞር ስብስቡን ሲያጠናክር ከርሟል።

የአሠልጣኝ አብርሃም ምክትሎች እስካሁን ተለይተው ባይታወቁም ክለቡ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ለመጀመር ነሐሴ 20 ተጫዋቾቹ እንደሚሰባሰቡ የክለቡ የቴክኒክ ዳይሬክተር መብራቱ ሀብቱ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በተባለው ቀን ተጫዋቾች ባህር ዳር ላይ ሪፖርት ካደረጉ በኋላ በ21 እና 22 የህክምና ምርመራ እንደሚደረግላቸው ሲገለፅ በቀጣይ ቀን ደግሞ ከጉዞ ስለመጡ እረፍት እንዲያደርጉ እንደረጋል ተብሏል። ነሐሴ 24 ላይ ግን ቡድኑ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በይፋ ዝግጅቱን እንደሚጀምርም ተመላክቷል።