ቡናማዎቹ አህጉራዊ ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት ቀን ታውቋል

ከአስር ዓመታት በኋላ ወደ አህጉራዊ ውድድር የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡና በቅድመ ማጣሪያ መርሐ-ግብር የዩጋንዳውን ዩ አር ኤ የሚገጥምበት የጨዋታ ቀን ታውቋል።

በአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በተጠናቀቀው የሊጉ ውድድር ሁለተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ለመወዳደር ዕድል እንዳገኙ ይታወቃል። ከቀናት በፊት በቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ተጋጣሚውን ያወቀው ክለቡም በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ የሚያደርገው ጨዋታ መቼ እንደሆነ ታውቋል።

በዚህም ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን መስከረም 2 ወደ ዩጋንዳ ተጉዞ በናምቦሌ ስታዲየም ሲያደርግ የመልሱን ጨዋታ ደግሞ ከሳምንት በኋላ መስከረም 9 ባህር ዳር ላይ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ ቡና ከፊቱ ለሚጠብቁት ወሳኝ ጨዋታዎች መቀመጫውን ቢሾፍቱ በማድረግ እየተዘጋጀ እንደሆነ ይታወቃል።