የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ሁለተኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ከሁለት ቀናት በኋላ ያከናውናል።
የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት 7 ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከወዲሁም ክለቦቹ ተጋጣኚዎቻቸውን አውቀው ዝግጅት እዬደረጉ ይገኛሉ። ሊጉን የሚያስተዳድረው የሼር ካምፓኒም ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ለመከወን የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 22 ቀጠሮ ይዟል፡፡
ሼር ካምፓኒው ለክለቦች በላከው ደብዳቤ እንዳሳወቀው ዓመታዊ ክንውን ሪፖርት እና ቀጤይ ዕቅድ በዋናነት የሚቀርቡ ሲሆን በተሰሩ ሥራዎች እና መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ላይም በስፋት ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው በዕለቱ 2፡30 ሲል በኢንተርኮንቲኔንታል እንደሚጀምርም ተጠቁሟል፡፡