የፊታችን ሀሙስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርገው የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ዋልያውን የሚገጥምበትን ስብስብ ይፋ ሲያደርግ አዲስ አበባ የሚገባበትም ሰዓት ታውቋል።
በአሠልጣኝ ጆን ኬይስተር የሚመራው የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አስተናጋጅነት ለሦስት ቀናት በሚከናወነው ውድድር ላይ ተሳታፊ እንደሚሆን ይታወቃል። ብሔራዊ ቡድኑ ከፊቱ ላለበት ንዑስ ውድድር አቋሙን ለመፈተሽ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የፊታችን ሀሙስ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል።
ከቤኒን ጋር በነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ህግ ጥሷል በሚል የ5 ሺ ዶላር ቅጣት በካፍ የተጣለበት ቡድኑም በኢትዮጵያ የአቋም መለኪያ ጨዋታ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውድድር የሚጠቀምበትን ስብስብ ይፋ አድርጓል። በዚህም አሠልጣኝ ጆን ኬይስተር ለሦስት የግብ ዘቦች፣ ሰባት ተከላካዮች እና አማካዮች እንዲሁም ለስድስት አጥቂዎችን በአጠቃላይ ለ23 ተጫዋቾችን ጥሪ ማድረጋቸው ታውቋል።
በአጠቃላይ 40 የልዑካን ቡድን በመያዝ በአሁኑ ሰዓት ጉዞ ላይ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደሚደርስ ሲገለፅ አዳሩንም አዲስ አበባ ላይ አድርጎ ነገ ወደ ባህር ዳር እንደሚያመራ ተጠቁሟል።
የቡድኑ ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው 👇