ኢትዮጵያ መድን አዲስ አሠልጣኝ ቀጥሯል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚወዳደረው ኢትዮጵያ መድን የቀድሞ አሠልጣኙን ዳግም ቀጥሯል።

በኢትዮጵያ ሁለተኛው የሊግ እርከን (ከፍተኛ ሊግ) የሚወዳደረው ኢትዮጵያ መድን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በምድብ ሐ 35 ነጥቦችን በመያዝ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በአሠልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ እየተመራ ያለፈውን የውድድር ዓመት ያሳለፈው ክለብ ከአሠልጣኙ ጋር ከተለያየ በኋላ የቀድሞ አሠልጣኙን ወደ መንበሩ መልሷል።

ክለቡን ለማሰልጠን የተሾሙት አሠልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ ናቸው። በተጠናቀቀው ዓመት ገላን ከተማን ሲያሰለጥኑ የነበሩት ወጣቱ አሠልጣኝ ከዚህ ቀደም በ2011 ኢትዮጵያ መድንን ይዘው ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ብርቱ ፉክክር አድርገው ነበር። ለዘንድሮ ውድድር ዓመት ክለቡን ለማሰልጠን ውል ያሰሩት አሰልጣኝ በፀሎት ከጫፍ ደርሰው ያጡትን ስኬት ዘንድሮ ለማሳካት የማለም ወደ ቀድሞ ክለባቸው ተመልሰዋል።

ያጋሩ