ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ላለበት የዓለም ከ20 አመት በታች ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት ለአርባ ተጫዋቾች ጥሪን አቅርቧል፡፡

ኮስታሪካ ለምስተናግደው የ2022 የአለም ከ20 ዓመት በታች የማጣሪያ ጨዋታዎች በአፍሪካ ዞን እየተደረጉ የሚገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከሩዋንዳ ጋር የማጣሪያ መርሀግብሩን በመስከረም ወር መጀመሪያ ያከናውናል፡፡ በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከነሐሴ 21 ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ ዝግጅታቸውን ማድረግ የሚጀምሩ ሲሆን ለዝግጅትም አሰልጣኙ ለአርባ ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡ ተጫዋቾቹም ከኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የተመረጡ ናቸው፡፡

ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ባንቺአየሁ ደመላሽ (ባህርዳር ከተማ)፣ መስከረም መንግሥቱ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ዓባይነሽ ኤርቄሎ (መከላከያ)፣ እየሩሳሌም ሎራቶ (አዳማ ከተማ)

ተከላካዮች

አብነት ለገሠ (አአ ከተማ)፣ ናርዶስ ዘውዴ (አዳማ ከተማ)፣ ታሪኳ ዴቢሶ (ንግድ ባንክ)፣ ብዙዓየው ታደሰ (ንግድ ባንክ)፣ ብርቄ አማረ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ፍሬወይኒ አበራ (ድሬዳዋ) ፣ መስከረም ኢሳይያስ (አርባምንጭ ከተማ)፣ ንግስት አስረስ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ማክዳ ዓሊ (አቃቂ)፣ ቤተልሄም በቀለ (መከላከያ)፣ ነፃነት ፀጋዬ (መከላከያ)፣ ትዕግስት ኃይሌ (ንግድ ባንክ)

አማካዮች

አረጋሽ ካልሳ (ንግድ ባንክ)፣ የምስራች ሞገስ (ወጣቶች አካዳሚ)፣ ማዕድን ሳህሉ (መከላከያ)፣ ቤቲ ዘውዴ (ኤሌክትሪክ)፣ ትሁን አየለ (ድሬዳዋ)፣ ፋና ዘነበ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ሲሳይ ገብረዋህድ (ሀዋሳ ከተማ)፣ መዓዛ አብደላ (ቦሌ)፣ ገነት ኃይሉ (መከላከያ)፣ መሳይ ተመስገን (መከላከያ)፣ ኤልሳቤት ብርሀኑ (መከላከያ)፣ እፀገነት ግርማ (መከላከያ)

አጥቂዎች

ቤተልሔም ታምሩ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ በሻዱ ረጋሳ (አዳማ ከተማ)፣ ፎዚያ መሐመድ (ንግድ ባንክ)፣ አርያት ኦዶንግ (ወጣቶች አካዳሚ)፣ ንግስት በቀለ (ወጣቶች አካዳሚ)፣ ፀጋነሽ ወራና (ንግድ ባንክ)፣ ዮርዳኖስ ምዑዝ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ እየሩሳሌም ወንድሙ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሄለን መሰለ (ድሬዳዋ)፣ ቱሪስት ለማ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ረድኤት አስረሳኸኝ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ዓይናለም አሳምነው (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)