ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ 1ኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ነገ 10፡00 ላይ በግዙፉ የባህርዳር ስታድየም ቲፒ ማዜምቤን ለሚያስተናግድበት ፍልሚያ የመጨረሻ ልምምዱን ከደቂቃዎች በፊት አደርጓል፡፡
ፈረሰኞቹ መቀመጫቸውን በአቫንቲ ሆቴል በማድረግ በጨዋታው የማይሰለፈው ሳላዲን ሰኢድን ጨምሮ 22 ተጫዋቾችን በመያዝ በሆቴሉ አቅራብያ በሚገኘው የአፄ ቴዎድሮስ ስታድየም ከማክሰኞ ጀምሮ ልምምድ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ዛሬ ረፋድ ላይም የመጨረሻ ልምምድ አድርገዋል፡፡
ቡድኑ በዛሬው ልምምዱ ፈጣን ቅብብሎችን የመቀባበል እና የመቀማት ልምምዶችን ሲሰራ የነበረ ሲሆን የቆሙ ኳሶችን እና ተሸጋሪ ኳሶችን የመጠቀም ልምምድንም በመስመር ተጫዋቾቹ አማካኝነት ሲያከናውን ተስተውሏል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳላዲን በርጊቾ እና ብሪያን ኡሞኒን በጉዳት ፣ ሳላዲን ሰኢድን ደግሞ ለካፍ ባለማስመዘግቡ ለነገው ጨዋታ የማይደርሱለት ሲሆን ሌሎቹ የቡድኑ አባላት ግን በተሟላ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጧል፡፡
ፈረሰኞቹ ለጨዋታው የሚጠቀሙባቸው 21 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-
ግብ ጠባቂዎች
ሮበርት ኦዶንካራ ፣ ዘሪሁን ታደለ ፣ ፍሬው ጌታሁን
ተከላካዮች
አሉላ ግርማ ፣ አለማየሁ ሙለታ ፣ አንዳርጋቸው ይላቅ ፣ ደጉ ደበበ ፣ አስቻለው ታመነ ፣ አይዛክ ኢሴንዴ ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ ፣ አበባው ቡታቆ ፣ ዘካርያስ ቱጂ
አማካዮች
ምንተስኖት አዳነ ፣ ምንያህል ተሸመ ፣ ተስፋዬ አለባቸው፣ ናትናኤል ዘለቀ ፣ በሃይሉ አሰፋ ፣ ራምኬል ሎክ
፣ አቡበከር ሳኒ
አጥቂዎች
ዳዋ ሁቴሳ ፣ አዳነ ግርማ ፣ ጎድዊን ቺካ