በቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያደርገው ንግድ ባንክ አሰላለፍ ታውቋል

ከቪሂጋ ኩዊንስ ጋር የሴካፋ ዞን የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ ታውቋል።

በግብፅ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የአፍሪካ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የቀጠናውን የማጣሪያ ውድድር ለማከናወን ወደ ኬንያ ያመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10 ሰዓት ሲል የመጀመሪያ ጨዋታውን ከቪሂጋ ኩዊንስ ጋር እንደሚያደርግ ይታወቃል። አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛውም በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታቸው ወደሜዳ ገብተው እንዲጫወቱ የመረጧቸውን ተጫዋቾች ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች።

የተጫዋች አደራደር ቅርፅ (4-3-3)

ግብ ጠባቂ

ታሪኳ በርገና

ተከላካዮች

ብዙዓየሁ ታደሰ
ሀሳቤ ሙሶ
ትዝታ ኃይለሚካኤል
ታሪኳ ዴቢሶ

አማካዮች

ሕይወት ደንጊሶ
እመቤት አዲሱ
ሰናይት ቦጋለ

አጥቂዎች

መዲና ዐወል
ሎዛ አበራ
አረጋሽ ካልሳ

ያጋሩ