ኢትዮጵያዊ ኮሚሽነር ወደ ኬንያ ያመራሉ

የፊፋ እና የካፍ የጨዋታ ታዛቢ ወደ ምስራቃዊቷ አፍሪካ ሀገር ይጓዛሉ።

በኢትዮጵያ በሴት እና በወንድ ሁለት ሁለት በድምሩ አራት የጨዋታ ታዛቢ ኮሚሽነሮች ይገኛሉ። ከነዚህ መካከል የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፀሀፊ የሆኑት ኢንስትራክተር ሰለሞን ገብረሥላሴ አንዱ መሆናቸው ይታወቃል። ኢንስትራክተር ሰለሞን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ የፊታችን ሐሙስ ነሐሴ 27 በናይሮቢ ከተማ በኬንያ እና ሉጋንዳ መካከል የሚከናወነው ጨዋታን በኮሚሽነርነት ለመምራት ዛሬ ወደ ሥፍራው እንደሚያቀኑ ሰምተናል። ሁለቱን ጎረቤት ሀገሮችን የሚመሩት ኮሚሽነሩ የጨዋታውም ዳኞች አራቱም ከሱዳን መሆናቸው ታውቋል።

ኢንስትራክተር ሰለሞን በኢትዮጵያ የተደረገው የሴካፋ ውድድርን ጨምሮ በርካታ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎች ላይ በኮሚሽነርነት እየሰሩ ይገኛሉ።

ያጋሩ