ተጨማሪ ሁለት ተጫዋች ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ ሆኗል

ከደቂቃዎች በፊት ሦስት ተጫዋቾችን የቀነሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን ከስብስቡ ውጪ አድርጓል።

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ዓርብ እና በቀጣዩ ሳምንት ባለው ማክሰኞ ከጋና እና ዚምባቡዌ ጋር ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል። ብሔራዊ ቡድኑ ሱራፌል ዳኛቸው፣ በዛብህ መለዮ እና ዊልያም ሠለሞንን ከስብስቡ ውጪ ማድረጉን ከደቂቃዎች በፊት የገለፅን ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ ተጫዋቾች እንደተቀነሰ አረጋግጠናል።

በዚህም የግብ ዘቡ ፍሬው ጌታሁን እና የአማካይ መስመር ተጫዋቹ ፍፁም ዓለሙ ወደ ጋና ከሚያመራው ስብስብ ውጪ መሆናቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል።

ያጋሩ