ከአሠልጣኝ ሳሙኤል አበራ ጋር የተለያየው አዳማ ከተማ አዲስ አሠልጣኝ ለማግኘት የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል።
የ2011 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ አዳማ ከተማ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከሻምፒዮኑ ንግድ ባንክ በ29 ነጥቦች ርቆ 7ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ለአራት ተከታታይ ዓመታት ክለቡን ያሰለጠኑት አሠልጣኝ ሳሙኤል አበራ ውላቸው መጠናቀቁን ተከትሎ መለያየታቸው ሲገለፅ ክለቡም አዲስ አሠልጣኝ ለመቅጠር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ድረ-ገፃችን ተረድታለች።
ክለቡ በትናንትናው ዕለት ባወጣው የአሠልጣኝ ቅጣር ማስታወቂያ ላይም የካፍ አልያም የፊፋ ኤ ላይሰንስ ያለው/ላት እንዲሁም በፕሪምየር ሊጉ ቢያንስ የስምንት ዓመት የስልጠና ልምድ ያለው/ላት ለመቅጠር መስፈርት አውጥቷል። ከቀናቶች በፊት አዳዲስ ተጫዋቾቹን ወደ ስብስቡ የቀላቀለውን ክለብ ለማሰልጠን የሚፈልጉ አመልካቾችም እስከ ጷጉሜ 1 ድረስ በጽሕፈት ቤት በመገኘት እንዲያመለክቱ ተጠቁሟል።
ክለቡ ያወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከስር ተያይዟል 👇